የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በጎንደር ከተማ ያቋቋመው ዘመናዊ የኤሌክትሮኒክስ ግብይት ማዕከል ተመረቀ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በጎንደር ከተማ ያቋቋመው ዘመናዊ የኤሌክትሮኒክስ ግብይት ማዕከል ተመረቀ
ጎንደር ፤ ጥር 27/2013(ኢዜአ) የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በጎንደር ከተማ በ14 ሚሊዮን 800 ሺህ ብር ወጪ ያቋቋመው ዘመናዊ የኤሌክትሮኒክስ ግብይት ማዕከል ዛሬ ተመርቆ ተከፈተ።
ማዕከሉ ለሀገሪቱ አራተኛው መሆኑንና በአንድ ጊዜ 90 ደንበኞችን ማገበያየት የሚያስችል መሆኑን የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወንድማገኝ ነገሬ በምረቃው ሥነ-ሥርዓት ወቅት ገልጸዋል።
በአካባቢው በስፋት የሚመረቱት ሰሊጥ፣ አኩሪ አተርና አረንጓዴ ማሾ የመሳሰሉ ምርቶች ለውጭ ለማቅረብ የሚያገለግል ዘመናዊ የኤሌክትሮኒክስ ግብይት ማዕከል እንደሆነ ተመልክቷል።
በምረቃው ሥነሥርዓት የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል እና የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አገኘሁ ተሻገር ጨምሮ ሌሎችም የፌዴራል፣ ክልል፣ ከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች፣ የንግዱ ማህበረሰብ ፣ ባለሀብቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸውን ሪፖርተራችን ከጎንደር ዘግቧል።