ቀጥታ፡

በጅማው የዛሬ የሊጉ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ሲዳማ ቡናን በሰፊ የጎል ልዩነት አሸነፈ

ጂማ ፤ ጥር 26/2013(ኢዜአ) በጅማ ዪኒቨርሲቲ ስታዲዮም ዛሬ በተካሄደው አስራ አንደኛው ሳምንት ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ሲዳማ ቡናን አምስት ለዜሮ አሸነፈ፡፡

ከእረፍት በፊት  ዜሮ ለዜሮ  የነበረው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ አቡበከር ናስር በ59ኛው፣ በ64ኛውና በ83ኛው ደቂቃ 3 ግቦችን ለኢትዮጵያ ቡና በማስቆጠር  ሀትሪክ ሰርቷል፡፡

የተቀሩትን ሁለት ጎሎች ሀብታሙ ታደሰ በ68ኛው እንዲሁም አስራት ቱንጆ በ90ኛው ደቂቃ አክሎ ኢትዮጵያ ቡና አምስት ለዜሮ ማሸነፍ ችሏል፡፡

ኢትዮጵያ ቡና በ20 ነጥብ የሁለተኛ ደረጃን ይዟል፡፡

በከፍተኛ ጎል አግቢ ተጨዋች ደረጃ ለሳምንታት በሙጂብ ቃሲም ተይዞ የነበረውን  አቡበከር ናስር ተረክቦታል፡፡

ነገ ረፋድ አራት ሰዓት  ላይ ባህርዳር ከተማ ከጅማ አባጅፋር እንደሚጫወቱ የሚጠበቅ መሆኑን ሪፖርተራችን ከጅማ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም