ቅዱስ ጊዮርጊስና ሃዲያ ሆሳዕና በዛሬው ጨዋታ አንድ እኩል ተለያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ቅዱስ ጊዮርጊስና ሃዲያ ሆሳዕና በዛሬው ጨዋታ አንድ እኩል ተለያዩ
ጅማ፣ጥር 26/2013( ኢዜአ) በአስራ አንደኛዉ ሳምንት ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ዛሬ 4 ሰዓት ላይ ሀዲያ ሆሳዕና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ 1ለ1 አቻ ተለያዩ፡፡
ከእረፍት በፊት ሁለቱም ቡድኖች ምንም ግብ ያላስቆጠሩ ሲሆን ከረፍት በኋላ ዳዋ ሁቴሳ በ76ኛዉ ደቂቃ ለሀዲያ ሆሳዕና ሲያስቆጥር ሄኖክ አዱኛ በ78ኛዉ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ግብ አስቆጥሯል፡፡
ሀዲያ ሆሳዕና ነጥቡን ወደ 19 ከፍ በማድረግ የሁለተኝነት ደረጃዉን እንዳስጠበቀ ቀጥሏል፡፡
ቅዱስ ጊዮርጊስ 18 ነጥብ ይዞ በ3ኛ ደረጃ ይከተለዋል፡፡