በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ እንደቀጠለ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ እንደቀጠለ ነው
ጅማ፤ ጥር 22/2013(ኢዜአ)፡- በቤትኪንግ አስረኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ በጅማ ዩኒቨርሲቲ ስቴዲዮም ዛሬም እንደቀጠለ ነው።
ዛሬ ረፋዱ ላይ የተገናኙት ቅዱስ ጊዮርጊስና ሲዳማ ቡና ዜሮ ለዜሮ ተለያይተዋል፡፡
ከሰዓት በኋላ ዘጠኝ ሰዓት ደግሞ ሰበታ ከተማ ከሀዲያ ሆሳእና ጋር እንደሚጫወቱ ይጠበቃል።
ትናንት በተደረገ ጨዋታ ወልቂጤ ከተማ ድሬዳዋን ሶሰት ለአንድ ሲያሸንፍ ኢትዮጵያ ቡና እና ባህርዳር ከነማ ሁለት ለሁለት ተለያይተዋል፡፡
በጨዋታው አሜ መሀመድ በ40ኛው ፣ አቡበከር ሳኒ በ75ኛው እና አብዱልከሪም ወርቁ ደግሞ በ90ኛው ደቂቃ ለወልቂጤ ግብ በማስቀጠር ነው ቡድኑ ያሸነፈው፡፡
ለድሬዳዋው ግብ ያስቆጠረው ደግሞ ሙሂዲን ነው።
ሚኪያስ መኮንን በስድስተኛው እና አቡበከር ናስር በ54ኛው ደቂቃ ለኢትዮጵያ ቡና ፤ፍጹም አለሙ እና ምንይሉ ወንድሙ በሶሰተኛው እና በ24ኛው ደቂቃ ግብ በማስቆጠር አቻ ሆነው ጨዋታው ተጠናቋል፡፡