ቀጥታ፡

በ10ኛው ቤትኪንግ ወልቂጤ ከነማ ሲያሸንፍ ኢትዮጵያ ቡናና ባህርዳር ከነማ ነጥብ ተጋርተዋል

ጂማ ኢዜአ ጥር 21/2013 (ኢዜአ ) ዛሬ በአስረኛዉ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ዛሬ 4 ሰዓት ላይ ወልቂጤ ከተማ 3-1 ድሬድዋን ሲያሸንፍ በዘጠኝ ሰአቱ ጨዋታ ደግሞ ኢትዮጵያ ቡናና ባህርዳር ከነማ 2ለ2 አቻ ሆነዋል፡፡

አሜ መሀመድ በ40ኛዉ ደቂቃ አቡበከር ሳኒ በ75ኛዉ እና አብዱልከሪም ወርቁ በ90ኛዉ ደቂቃ ለወልቂጤ አስቆጥረዉ በድል ወተዋል፡፡

የድሬድዋዉ ሙሂዲን በ75ኛዉ ደቂቃ ግብ ቢያስቆጥርም ቡድኑን ከሽንፈት አላዳነዉም፡፡

በከሰአቱ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡናና ባህርዳር ከነማ 2ለ2 አቻ ሆነዉ አጠናቀዋል፡፡

ሚኪያስ መኮንን በ6ኛዉ እና አቡበከር ናስር በ54ኛዉ ለኢትዮጵያ ቡና ሲያስቆጥሩ ፍጹም አለሙና ምንይሉ ወንድሙ በ3ኛዉ እና በ24ኛዉ ደቂቃ ግብ በማስቆጠር አቻ ሆነዉ ጨዋታዉ ተጠናቋል፡፡

አስረኛዉ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየርሊግ ጨዋታ ነገም የሚቀጥል ይሆናል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም