ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የሰው ሰራሽ አካልና የአካል ድጋፍ ማደራጃ ድርጅትን ጎበኙ

ጥር 20/2013 ( ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በዛሬው እለት በጤና ሚኒስትር የሰው ሠራሽ አካልና የአካል ድጋፍ ማደራጃ ድርጅትን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝታቸውም በሕግ ማስከበር ሂደቱና በሌሎችም ጊዜያት የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች በጎ ፈቃደኞችና የሰው ሠራሽ አካል ማምረቻ ድርጅት ባለሙያዎች የሚደነቅ ሥራ እየሠሩ መሆኑን ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚንስትሩ ለተጎዱ የመከላከያ ሠራዊት አባላትና ለሲቪሎች የሚሠራውን ሰው ሠራሽ አካል በጎበኙበት ወቅት " ከውጭ መጥተው በበጎ ፈቃደኝነት ይሄንን ታላቅ ሥራ የሚሠሩ ሰሎሞን አማረን የመሰሉ ወገኖች ሊበረታቱ ይገባል" ብለዋል።

ድርጅቱ ሰው ሰራሽ አካል እና ለመንቀሳቀስ ድጋፍ የሚሆን እንደ ክራንች ያሉትን እና ሰው ሰራሽ አካላትን በማምረት ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም