በላልይበላ የፌዴራል፣ የክልልና የከተማ አስተዳደሮች ምክር ቤቶች የጋራ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው

ላልይበላ፤ ጥር 17/2013(ኢዜአ) የፌዴራል፣ የክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች ምክር ቤቶች የጋራ የምክክር መድረክ በላልይበላ እየተካሄደ ነው።

በምክክር መድረኩ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድና ባለፉት ሁለት ዓመታት የተከናወኑ የለውጥ ተግባራት ቀርበው ውይይትም ይካሄድባቸዋል ተብሏል።

በተመሳሳይ የፌዴሬሽን ምከር ቤት የለውጥ ተግባራት ቀርበው በተሳታፊዎች ይመከርባቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።

ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት በሚካሄደው የውይይት መድረክ በረቂቅ ሕጎችና ሌሎች ጉዳዮችም ምክክር ይደረጋል ተብሏል።

የፌዴራል፣ የክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች ምክር ቤቶች የጋራ የምክክር መድረክ በዓመት ሁለት ጊዜ የሚካሄድ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም