በምዕራብ ጎጃም ዞን ዓመታዊ የባህል ስፖርቶች ውድድር ተጀመረ

ባህርዳር ጥር 14/2013 (ኢዜአ) በምዕራብ ጎጃም ዞን 18ኛው ዓመታዊ የባህል ስፖርቶች ውድድር ዛሬ በአዴት ከተማ ተጀመረ።

እስከ ጥር 22/013 ዓ.ም. ድረስ በሚቆየው ውድድር  ከዞኑ 14 የገጠር ወረዳዎችና  ሁለት የከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ ከ650 የሚበልጡ  ስፖርተኞች በውድድሩ እንደሚሳተፉ ይጠበቃል።

ዓላማው በቀጣዩ ወር መግቢያ በኮምቦልቻ ከተማ በሚካሄደው ክልል  አቀፍ  የባህል  ስፖርቶች ውድድርና ፌስቲቫል የሚሳተፉ ተወዳዳሪዎችን ለመምረጥ ነው።

የዞኑ ስፖርት ተጠሪ ጽህፈት ቤት ተወካይ አቶ መለሰ ስንሻው  የባህል ስፖርቶች ውድድር  ያሉንን ባህላዊ እሴቶች እርስ በእርስ በመለዋወጥ ማህበራዊ ትስስራችንን እንዲጠናከር ያደርጋል ብለዋል።

በውድድሩ ፈረስ ጉግስ፣ ገበጣ፣ ትግል፣ የገና ጨዋታን  ጨምሮ 11  የተለያዩ የባህል  ስፖርቶች እንደሚካሄዱ አስረድተዋል

ስፖርቱን ህዝባዊ መሰረት እንዲኖረው ለማስቻል  በሚከናወነው ተግባራት የሚስተዋሉ  ክፍተቶችን ለይቶ በማረም በቀጣይ እንዲስተካከል  ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ እየሰሩ እንደሚገኙ ማስታወቃቸውን የዞኑ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አንማው ዳኛቸው ለኢዜአ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም