የኢትዮጵያ የመጀመሪያው የሴቶች ቮሊቦል ክለቦች የጥሎ ማለፍ ውድድር ይካሄዳል - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ የመጀመሪያው የሴቶች ቮሊቦል ክለቦች የጥሎ ማለፍ ውድድር ይካሄዳል
አዲስ አበባ፣ ጥር 14 ቀን 2013 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ የመጀመሪያው የሴቶች ቮሊቦል ክለቦች የጥሎ ማለፍ ውድድር ነገ እንደሚጀመር ፌዴሬሽኑ አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ቮሊቦል ፌዴሬሽን እንደገለፀው በአዲስ አበባ ትንሿ ሁለገብ ስታዲየም በሚካሄደው ውድድር ጌታዘሩ ስፖርት ክለብ፣ ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ፣ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲና ፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ይሳተፋሉ።
ነገ ጠዋት በሚካሄደው የመክፈቻ ውድድር በቅድሚያ ፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ከወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ይጫወታሉ።
በመቀጠልም ጌታዘሩ ስፖርት ክለብና ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ ጋር ይገናኛሉ።
ውድድሩ እስከ ጥር 17 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ እንደሚዘልቅ ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።