በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ የህዝብ የሰላም ኮንፍረንስ እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ የህዝብ የሰላም ኮንፍረንስ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥር 14/2013 ( ኢዜአ) በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ የህዝብ የሰላም ኮንፍረንስ እየተካሄደ ነው፡፡
በመተከል ማንነትን መሰረት ባደረገው ጥቃት ንጹሐን ዜጎች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውና ንብረት መውደሙ ይታወሳል፡፡
በመሆኑም አካባቢው ወደ ቀደመ ሰላምና መረጋጋት ተመልሶ ዜጎች ከስጋት ነፃ ሆነው መኖር በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ግብረ ሃይሉ ህዝቡን በማወያየት ላይ ይገኛል።
ከዳንጉር ወረዳ ሁሉም ቀበሌዎች የተውጣጡ ነዋሪዎችም በውይይቱ ላይ ተሳትፈዋል።
የሰላም ኮንፍረንሱ በሀገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ቡራኬ ተጀምሯል።