በአፋር ክልል የጋላፊ ዲቾቶ መገንጠያ ኤሊዳር በሌሆ አስፋልት ሲሚንቶ ኮንክሪት መንገድ ተመረቀ

123

አዲስ አበባ፣ ጥር 13/2013(ኢዜአ)  በአፋር ክልል የጋላፊ ዲቾቶ መገንጠያ ኤሊዳር በሌሆ አስፋልት ሲሚንቶ ኮንክሪት መንገድ ተመረቀ።

በአፋር ክልል የጋላፊ ዲቼቶ መገንጠያ መንገድ የክልሉ ፕሬዚዳንት አወል አርባ፣ የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ዳግማዊት ሞገስ እና ከፍተኛ የፌዴራልና የክልል የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ተመርቋል።

መንገዱ 78 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን ግንባታው 4 አመት ተኩል መፍጀቱ ተገልጿል፡፡

ለግንባታው 2 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ወጪ እንደተደረገበትም እንዲሁ፡፡

መንገዱ ኢትዮጵያ የታጁራ ወደብን በመጠቀም ከፍ ያለ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም እንድታገኝ ትልቅ እድል የሚፈጥር መሆኑም ተነግሯል።

ከዚህ ባለፈ የመንገዱ መገንባት በጋላፊ መስመር ያለውን የትራፊክ መጨናነቅ ከ50 በመቶ በላይ ለመፍታት ያስችላል፡፡

በተያያዘም ሜሎዶኒ መገንጠያ ማንዳ ቡሬ የአስፋልት ሲሚንቶ ኮንክሪት መንገድ ግንባታ መሰረተ ድንጋይ ተቀምጧል፡፡

መንገዱ 71 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውና 2 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ወጪ እንደሚደረግበት ተገልጿል፡፡

የመንገዱ መገንባት ወደ አሰብ ወደብ ለመግባት ከፍተኛ ጥቅም ያለው መሆኑም ተነግሯል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም