በስምንተኛው ሣምንት የሊጉ ውድድር ሃዋሳ ከተማ ሲዳማ ቡናን አሸነፈ

72

አዲስ አበባ ጥር 12/2013 (ኢዜአ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ሃዋሳ ከተማ ሲዳማ ቡናን 2 ለ 0 አሸንፏል።

በስምንተኛው ሣምንት የሊጉ ጨዋታ ለሃዋሳ ከተማ የማሸነፊያ ጎሎችን ያስቆጠሩት ብሩክ በየነ እና መስፍን ታፈሰ ናቸው።

የኢትዮጵያ የቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ከሠዓት በኋላ የሚቀጥል ሲሆን ፋሲል ከነማ ከአዳማ ከተማ የሚጫወቱ ይሆናል።

በዚህ ጨዋታ ፋሲል ከነማ  ካሸነፈ ነጥቡን 19 በማድረስ መሪነቱን አስጠብቆ የሚቀጥል ይሆናል፤ አዳማ ከተማ ፋሲልን ካሸነፈ ደግሞ ለጊዜውም ቢሆን አዳማ ከወራጅ ቀጠና ይወጣል።

በኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ እሳከሁን በተካሄዱ ጨዋታዎች ፋሲል ከተማ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስና ባሕርዳር ከተማ በቅደም ተከተል ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ያለውን ደረጃ ይዘው እየመሩ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም