የጥምቀት በዓል የጸሎት ስነ-ስርዓት እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የጥምቀት በዓል የጸሎት ስነ-ስርዓት እየተካሄደ ነው
ጥር 11/ 2013 (ኢዜአ) የጥምቀት በዓል የጸሎት ስነ-ስርዓት እየተካሄደ ነው።
በኢትዮጵያ በየአመቱ ጥር 11 ቀን በሚከበረው የጥምቀት በዓል በታቦታት ማደሪያዎች ጥምቀተ ባህር ዙሪያ የጸሎት ስነ-ስርዓት እየተካሄደ ነው።
በአዲስ አበባ ጃንሜዳም እንዲሁ የጸሎት ስነ-ስርዓት እየተካሄደ ሲሆን በርካታ ምዕመናን ታድመዋል።
በስነ-ስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ አቡነ ማቲያስን ጨምሮ ብጹአን አባቶች ተገኝተዋል።
የግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ብጹአን አባቶች እንዲሁም የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
የጥምቀት ክብረ በዓል በሰው ልጅ ወካይ የማይዳሰስ ባህላዊ ቅርስ ሆኖ በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) መመዝገቡ ይታወቃል።