በጅማ ከተማ የንግድ ትርኢት ተከፈተ

ጅማ ፤ጥር 10 /2013 (ኢዜአ) በጅማ ከተማ 10ኛው የንግድ ትርኢት እና ባዛር ዛሬ ተከፈተ።

በዝግጅቱ  ከ80 በላይ ነጋዴዎች መሳተፋቸውን የጅማና አካባቢዋ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት   ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ነጂብ ከድር  ገልጸዋል።

እየተሳተፉ ያሉት ከጅማ፣ ወልቂጤ፣አዲስ አባበ፣ ሆሳእና ሌሎችም ከተሞች የመጡ ነጋዴዎች እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡

የንግድ ትርኢት እና ባዛሩ ዓላማ ምርትና አገልግሎትን ከተጠቃሚዎች ጋር በማገናኘት ግብይት መፍጠር መሆኑ ተገልጿል፡፡

ሸማቾች የሀገር ውስጥና  ውጭ ምርቶችን በአንድ ቦታ እንዲያገኙ የሚያስችል በመሆኑ ለአካባቢው ህብረተሰብም ሆነ ለነጋዴዎች የጎላ ጠቀሜታ እንደሚኖረውም ተመልክቷል፡፡

የንግድ ትርኢት እና ባዛሩ ከዛሬ ጀምሮ ለአስራ አምስት ቀናት የሚቆይ መሆኑን ሪፖርተራችን ከጅማ ዘግቧል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም