በከተራ በዓል ታቦታቱ ከመቅደሳቸው ወደ ባሕረ ጥምቀት እያመሩ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በከተራ በዓል ታቦታቱ ከመቅደሳቸው ወደ ባሕረ ጥምቀት እያመሩ ነው
አዲስ አበባ ጥር 10/2013 (ኢዜአ) በከተራ በዓል ታቦታቱ ከመቅደሳቸው ወደ ባሕረ ጥምቀት እያመሩ ነው።
በአዲስ አበባ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ምዕመናኑ ታቦታቱን በእልልታና በሆታ፤ ካህናቱ በአኮቴት (ምስጋና) እና ሽብሸባ ታቦታቱን ወደ ባሕረ ጥምቀት እየሸኙ ነው።
የታቦታቱ ወደ ባሕረ ጥምቀት የመውረዳቸው ምስጢር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሐይማኖት አማኞች ዘንድ እየሱስ ክርስቶስ ወደ ባሕረ ዮርዳኖስ ወርዶ በዮሐንስ ዕጅ ስለመጠመቁ ትዕምርት ተደርጓል ይወስዳል።
ከተራ በድምቀት ከሚከበርባቸው ስፍራዎች አንዱ በሆነው ጃንሜዳ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክረስቲያን ፓትሪያሪክ ብጹዎ አቡነ ማትያስን ጨምሮ ብፁዓን አባቶችና እንግዶች ታድመዋል።
በዓለም የማይዳሰስ ወካይ ቅርስነት የተመዘገበው የጥምቀት በዓል በነገው ዕለት በመላ ኢትዮጵያ በአማኞች ዘንድ በድምቀት ይከበራል።