ፋሲል ከነማ ዛሬ ሀድያ ሆሳዕናን በማሸነፉ በ16 ነጥብ የፕሪሚየር ሊጉ መሪ ሆነ

67

ጅማ፣ ጥር 09 ቀን 2013 (ኢዜአ) ዛሬ 4 ሰዓት ላይ በተካሄደው ሰባተኛው ሳምንት የቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ፋሲል ከነማ ሀዲያ ሆሳዕናን 1 ለ 0 አሸነፈ።

ፋሲል ከነማ ለአሸናፊነት የበቃው በ80 ኛው ደቂቃ ሙጂብ ቃሲም ባስቆጠራት ጎል ነው።

በጅማ ስታዲየም በቀጠለው የቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ፋሲል ከነማ ዛሬ ባገኘዉ ድል አማካኝነት በ16 ነጥብ ፕሪሚየር ሊጉን እየመራ ነው፡፡

ሀዲያ ሆሳዕናና ፋሲል ከነማ ፕሪሚየር ሊጉን ከፊት እየመሩ ያሉ ተፎካካሪ ክለቦች በመሆናቸው የዛሬው ጨዋታቸው ይጠበቅ ነበር፡፡

ሀዲያ ሆሳዕናና ኢትዮጵያ ቡና በተከታታይ በ13 ነጥብ በጎል ልዩነት ብቻ ተበላልጠው ሁለተኛና 3ኛ ደረጃን ይዘዋል፡፡

ዛሬ ዘጠኝ ሰአት ላይ አዳማ ከተማ ከወልቂጤ ከተማ ጋር ይጫወታሉ፡፡

ወልቂጤ ከተማ ዘጠኝ ነጥብ በመሰብሰብ 7ኛ ደረጃ ላይ ሲገኝ አዳማ ከተማ ደግሞ 4 ነጥብ ይዞ 11ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም