የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት እስከ ሐምሌ 25 ድረስ ይገለጻል

133
አዲስ አበባ ሃምሌ16/2010 የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት እስከ ሐምሌ 25 ቀን 2010 ዓ.ም ባለው ጊዜ ይፋ እንደሚደረግ የአገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አስታወቀ። የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ገብረእግዚአብሔር ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት እስከ ሐምሌ 25 ቀን 2010 ዓ.ም ባሉ ቀናት ውስጥ ይገለጻል። የ10ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ደግሞ የ12ኛ ውጤት ከታወቀበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ነሐሴ 25 ቀን 2010 ዓ.ም ይፋ እንደሚደረግም ጠቁመዋል። የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ብሄራዊ ፈተና ከግንቦት 27 ጀምሮ እስከ ግንቦት 30 2010 ዓ.ም ድረስ መሰጠቱ የሚታወስ ነው። በዘንድሮው ዓመት 284 ሺህ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስደዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም