ቀጥታ፡

የህግ ማስከበር ዘመቻ ላይ ለተሳተፉ የኦቢኤን ጋዜጠኞች የዕውቅና አሠጣጥ ፕሮግራም እየተካሄደ ነው

አዳማ ጥር 8/2013 (ኢዜአ) በትግራይ ክልል በተካሄደው የህግ ማስከበር ዘመቻ ሂደት ከሥፍራው መረጃን ለህዝብ በማድረስ ለተሳተፉ የኦቢኤን ጋዜጠኞች የዕውቅና አሠጣጥ ፕሮግራም እየተካሄደ ነው።

በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ባለው የዕውቅና አሠጣጥ ፕሮግራም ላይ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳና ምክትል ፕሬዚዳንት ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ ተገኝተዋል።

የኢፌዴሪ አየር ሃይል አዛዥ ሜጄር ጄኔራል ይልማ መርዳሳ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ቃል አቀባይ አምባሳደር ሬድዋን ሁሰን፣ የመከላከያ የሚዲያና ኢንዶክትርኔሽን ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል መሀመድ ተሰማ እና የተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን አመራሮችም በፕሮግራሙ ሥነ-ሥርዓት ላይ ታድመዋል።


የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም