በአዲስ ወግ የቆላማ አካባቢዎች የአርብቶ አደሮች የልማት ጉዞ ላይ ያተኮረ ውይይት እየተካሄደ ነው

57

አዲስ አበባ፤ ጥር 6/2013(ኢዜአ) በአዲስ ወግ የቆላማ አካባቢዎች የአርብቶ አደሮች የልማት ጉዞ ላይ አተኩሮ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ውይይት እየተካሄደ ነው።

በውይይቱ ባለፉት 15 አመታት በአርብቶ አደር ልማት ፖሊሲ ትግበራ የተገኙ ውጤቶችና ያጋጠሙ ክፍተቶች ይነሳሉ።

በመድረኩ ላይ በግብርና ሚኒስቴር የሰብል ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ማንደፍሮ ንጉሴ እና በዘርፉ የተለያዩ ኤክስፐርቶች የውይይት መነሻ ፅሁፎችን በማቅረብ ላይ ናቸው።

በአርብቶ አደር ልማት ፖሊሲ ትግበራ ስኬቶችና ተግዳሮቶች ላይ በመድረኩ ሰፊ ውይይት እንደሚደረግም ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም