በደቡብ ወሎ ከአንድ ቢሊዮን 600ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነቡ ፕሮጀክቶች ዛሬ እና ነገ ይመረቃሉ - ኢዜአ አማርኛ
በደቡብ ወሎ ከአንድ ቢሊዮን 600ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነቡ ፕሮጀክቶች ዛሬ እና ነገ ይመረቃሉ
ደሴ፤ጥር 6/2013 (ኢዜአ) በደቡብ ወሎ ዞን ከአንድ ቢሊዮን 600ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነቡ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች ዛሬ እና ነገ እንደሚመረቁ ተገለጸ።
የዞኑ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ሃላፊ አቶ ሰኢድ አህመድ ለኢዜአ እንደገለጹት ዛሬ ከሚመረቁት ፕሮጀክቶች መካከል የይስማ ንጉስ ሙዚየም፣ የሐይቅና ከላላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች ይገኙበታል።
የጨለቃና አጀዋ ድልድዮች፤ ትምህርት ቤትና የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶችም እንዲሁ።
ነገ ደግሞ የኮምቦልቻ ጠቅላላ ሆስፒታልና ዘመናዊ የቄራን ጨምሮ ሌሎችን መሰረተ ልማቶች እንደሚመረቁ ሃላፊው ገልጸዋል።
በመንግስት ወጪ የተገነቡት ፕሮጀክቶቹ የህብረተሰቡ የዘመናት የልማት ጥያቄዎችን ለመመለስ የሚያግዙ መሆናቸውን አስረድተዋል።
በፕሮጀክቶቹ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ከፌደራል፣ ክልልና ደቡብ ወሎ ዞን የተውጣጡ ከፍተኛ አመራሮች፣ የአካባቢው ነዋሪዎችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት እንደሚገኙ ይጠበቃል።