ቀጥታ፡

የአሰብ ወደብን መጠቀም የተለያየ ጠቀሜታ እንዳለው ተገለፀ

አዲስ አበባ ሐምሌ 16/2010 ኢትዮጵያና ኤርትራ  የአሰብ ወደብን ለመጠቀም መስማማታቸው  መልካም መሆኑን የከባድ ጭነት አሽከርካሪዎችና ባለንብረቶች ገለጹ። የአሰብን ወደብን መጠቀሙ ለአሽከርካሪና ለባለንብረቶች የትራንስፖርት አማራጭን ከማስፋት ባለፈ ለአገር የኢኮኖሚ ዕድገት አስተዋጽኦ ይኖረዋል። አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ ባለንብረቶችና አሽከርካሪዎች እንደተናገሩት፤ የኢትዮጵያና ኤርትራ ዳግም ወደ ሰላም መምጣት የትራንስፖርት አማራጩን ከማስፋት አንጻር ጠቀሜታው የጎላ ነው። አቶ ክፍሉ አስፋው የተባሉ አስተያየት ሰጪ  የወደቡ ስራ መጀመር ተቀዛቅዞ የነበረውን የደረቅ ጭነት የስራ እንቅስቃሴ የሚያነቃቃ መሆኑን ገልጸው የአሰብ ወደብ ለአዲስ አበባ ያለው ቅርበት ጊዜንና ወጪን እንደሚቀንስ ተናግረዋል፡፡ የከባድ መኪና አሽከርካሪው  ይልማ ደምሴ  እንዳሉት በአሰብ ወደብ መጠቀም ከህብረተሰቡ ጋር በባህል፣ በሃይማኖትና በሌሎች ማህበራዊ ጉዳይ ተመሳሳይነት ስለሚኖረው የተሻለ መግባባትና መናበብ ይኖራል። ከዚህ በተጨማሪም ለሁለቱ አገራት የእርስ በእርስ ግንኙነትና የንግድ ልውውጥ  ማደግ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ነው ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ። ከዚህ በተጨማሪም ለሁለቱ አገራት የእርስ በእርስ ግንኙነትና የንግድ ልውውጥ  ማደግ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ነው ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ። ኢትዮጵያና ጅቡቲ የአሰብ ወደብን በጋራ ለመጠቀም በሁለቱ አገሮች መሪዎች ከስምምነት መደረሱ ይታወቃል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም