ረቂቅ አዋጁ የሚዲያ ኢንዱስትሪውን ለመገንባትና ሙያን መሰረት አድርጎ ብዝሃነትን ለማንጸባረቅ ፋይዳ አለው... ጠቅለይ አቃቤ ህግ

69

አበባ፤ ጥር 3/2013(ኢዜአ) የመገናኛ ብዙሃን ረቂቅ አዋጅ ሙያን መሰረት በማድረግ በነጻነትና በሃላፊነት ብዝሃነትን ለማንጸባረቅና የሚዲያ ኢንዱስትሪውን ለመገንባት ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረው ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ገለፀ።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ፣ የፍትህና የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ረቂቁን ላቀረቡትና ለሚመለከታቸው ሃላፊዎች ጥያቄዎች አቅርቧል።

በረቂቅ አዋጁ የተካተቱ አዋጆች፣ አንቀጾች፣ ድንጋጌዎችና ይዘቶች ላይ መካተትና ግልጽ መሆን አለባቸው የተባሉ ጥያቄዎችም የቋሚ ኮሚቴው አባላት አንስተዋል።

ለተነሱት ጥቄዎችም የሚመለከታቸው አካላት ማብራሪያና ምላሽ ሰጥተዋል።

ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ የረቂቅ አዋጁን ይዘትና ዓላማ አብራርተዋል።

ረቂቅ አዋጁ በሕገ-መንግስቱ እውቅና የተሰጣቸውን ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ፣ የፕሬስና የመገናኛ ብዙሃን ነጻ መብትን ተገቢ በሆነ ተቋማዊና ሕጋዊ ጥበቃ እንዲያገኝ ለማድረግ መዘጋጀቱን አብራርተዋል።

በመሆኑም መገናኛ ብዙሃን ሙያን መሰረት በማድረግ ብዝሃነትን ለማንጸባረቅ ጠንካራ ተቋም በመፍጠር የሚንቀሳቀሱበት ምህዳር ለመፍጠር ጉልህ ፋይዳ ይኖረዋል ተብሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም