በትግራይ ክልል ለሚገኙ ክለቦች እየተጫወቱ ላሉ ተጫዋቾች የተፈቀደው ልዩ የዝውውር ጊዜ ተራዘመ

58

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 30/2013 ( ኢዜአ) በትግራይ ክልል ለሚገኙ ክለቦች እየተጫወቱ ላሉ ተጫዋቾች የተፈቀደው ልዩ የዝውውር ጊዜ ተራዘመ። 

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በትግራይ ክልል ላሉ ክለቦች እየተጫወቱ ለሚገኙች ተጫዋቾች ልዩ የዝውውር ጊዜ ከታኅሣሥ 26 እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ለአምስት የሥራ ቀናት መፍቀዱ ይታወሳል።

ይሁን እንጂ ፌደሬሽኑ የፈቀደው ልዩ ዝውውር በገና በዓል ምክንያት ማራዘሙን አሳውቋል።

ፌዴሬሽኑ ከታኅሣሥ 26 እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ለአምስት የሥራ ቀናት የተፈቀደው ልዩ የዝውውር ጊዜ እስከ ጥር 3 ቀን 2013 ዓ.ም ነው ያራዘመው።

በመሆኑም ክለቦችና ተጫዋቾች የዝውውር ጊዜው ተጨማሪ ቀናት መፈቀዱን አውቀው ክለቦች ተጫዋቾችን ማስፈረም እንደሚችሉ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም