በሃሺሽ አዘዋዋሪነት የተጠረጠሩ አስር ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

26

አሶሳ፣ ታህሳስ 30 / 2013( ኢዜአ) በአሶሳ ከተማ አራት ኪሎ ግራም የሚጠጋ አደንዛዥ እፅ ሲያዘዋውሩ ነበር ያላቸውን አስር ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ፖሊስ አስታወቀ። 

የከተማዋ  አስተዳደር  ፖሊስ መምሪያ ተወካይ ምክትል ኢንስፔክተር ደረጀ ኢታና ለኢዜአ እንደተናገሩት ትናንት ማምሻውን  በቁጥጥር ሥር የዋሉት ተጠርጣሪዎቹ ሃሺሹ ተገኝቶባቸው ነው፡፡

ሃሺሹ የተገኘው ከጉዳዩ ጋር ተጠርጥሮ በቁጥጥር ሥር ከዋለ አንድ ግለሰብ ቤት ፖሊስ በተደረገው ፍተሻ  እንደሆነ አመልክተዋል፡፡

ከአደንዛዥ እጹ አዘዋዋሪ ግለሰብ ጋር ቀጥታ ግንኙነት እንዳላቸው ፖሊስ የደረሰባቸው ሌሎች ዘጠኝ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር እንዳዋለ ምክትል ኢንስፔክተር ደረጀ አስታውቀዋል፡፡

ካናቢስ መሰል አደንዛዥ እፅ የሆነው የሃሺሹ ናሙና ለተጨማሪ ምርመራ ወደ ፌደራል ፖሊስ ፎረንሲክ የምርመራ ማዕከል መላኩን አስረድተዋል።

በቅርቡ በህገወጥ መንገድ መሰል አደንዛዥ እጽ በቁጥጥር ሥር እንደዋለም አስታውሰዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም