የኢትዮጵያና ኤርትራ የሰላም ግንኙነት የሁለቱን ህዝቦች ጥቅም እንዲያስከብር እንሰራለን---የትግራይ ተወላጅ ምሁራን

66
መቀሌ ሐምሌ 15/2010 የተጀመረው የኢትዮጵያና ኤርትራ የእርቅና የሰላም ሒደት ዘላቂ ለማድረግ የሁለቱንም ህዝቦች ጥቅም በሚያስጠብቅ መልኩ እንዲተገበር እንደሚያግዙ የትግራይ ተወላጅ ምሁራን ገለጹ። ምሁራኑ ላለፉት አምስት ቀናት በመቀሌ ከተማ ሲያካሒዱት የቆየውን ኮንፈረንስ ባለ ስምንት ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት አጠናቀዋል። በአቋም መግለጫቸው እንዳመለከቱት የክልሉን የልማት ስራዎች ለማጠናከር በሚደረገው ጥረት ውስጥ የበኩላቸው አስተዋጽኦ ለማበርከት ዝግጅት አድርገዋል። በመላው ሃገሪቱ እየተካሔደ ያለው የለውጥ ጉዞ የሁሉንም ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ መልኩ እንዲከናወን አስፍላጊውን እገዛ እንደሚያደርጉም በመግለጫቸው አመልክተዋል። በኮንፈረንሱ ላይ ከመላው አለም የተወጣጡ ከ1ሺህ 300 በላይ የክልሉ ተወላጅ ምሁራን ተሳትፈዋል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም