ሜሪጆይ ኢትዮጵያ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ለተቸገሩ ወገኖች ድጋፍ አደረገ

63

አርባ ምንጭ፣  ታህሳስ 29/2013 (ኢዜአ) ሜሪጆይ ኢትዮጵያ አርባ ምንጭ ቅርንጫፍ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ችግረኛ ለሆኑ 76 ወገኖች ድጋፍ አደረገ፡፡

የቅርንጫፉ አስተባባሪ አቶ ምንተስኖት ወንድወሰን እንደገለጹት፤ ድጋፍ የተደረገላቸው አረጋዊያንና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ህብረተሰብ ክፍሎች ናቸው።

የተደረገላቸው ድጋፍ ብርድ ልብስ፣ የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል መሆኑን አስረድተዋል።

የአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ይስሃቅ አብርሃም በበኩላቸው ሜሪጆይ ኢትዮጵያ ከአረጋውያን ጋር በተያያዘ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

"በከተማዋ ስራ ከጀመረ ወዲህ በሺዎች የሚቆጠሩ አረጋዊያንና አጋዥ የሌላቸውን ወገኖች በተለያየ መንገድ ድጋፍ ሲያደርግ ቆይቷል" ብለዋል።

ከተማ አስተዳደሜሪጆይ ለሚያከናውናቸው ተግባራት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም