ቀጥታ፡

ሀገር አቀፍ የሠላም ውይይት በአሶሳ ከተማ ተጀመረ

አሶሳ፤ታህሳስ 28/2013(ኢዜአ) የኢትዮጵያ የሃይማኖት ጉባኤ ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር በመተባባር ያዘጋጀው ሀገር አቀፍ የሠላም ውይይት ዛሬ በአሶሳ ከተማ ተጀመረ።

ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ከተወጣጡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር የሚካሄደው ውይይት በአካባቢውና በሀገሪቱ ጸጥታ ጉዳይ ላይ ያተኮረ ነው።

ለአንድ ቀን በሚቆየው በዚሁ ውይይት የተለያዩ ሃይማኖት ተቋማት ከፍተኛ አመራሮችም እየተሳተፉ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም