በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበሩ የጦር መሳሪያዎች ተያዙ

93

ደሴ፣ ታህሳስ 25/2013 (ኢዜአ) በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 3 ሺህ 474 ተተኳሽ ጥይትና ሌሎች የጦር መሳሪያዎችን መያዙን በፌደራል ጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ አስታወቀ፡፡ 

በቅርንጫፉ የደንበኞች ትምህርት ክፍል ቡድን አስተባባሪ አቶ አሳምነው አዳነ ለኢዜአ እንደገለጹት ተተኳሽ ጥይቶቹና ሌሎች የጦር መሳሪያዎች የተያዙት ትናንት በወልድያ ጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ድንገት በተደረገ ፍተሻ ነው።

የጦር መሳሪያዎቹ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-24011 አማ በሆነ አነስተኛ የህዝብ ማመላለሻ በድብቅ ተጭነው  ከሃራ ወደ ወልድያ ሊገቡ ሲሉ መያዛቸውን ተናግረዋል።

በፍተሻው ከተተኳሽ ጥይቶች በተጨማሪ አንድ ሽጉጥ መያዙንም ጠቅሰዋል።

አሽከርካሪውና ረዳቱ ለጊዜው በመሰወራቸው በፖሊስ ክትትል እየተደረገባቸው መሆኑን አስተባባሪው አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም