በግብርና ስኬት ላስመዘገቡ አርሶና አርብቶ አደሮች ዕውቅናና ሽልማት እየተሰጠ ነው

44

አዳማ፣ ታህሳስ 25/2013 ( ኢዜአ) በኦሮሚያ ክልል በግብርና ዘርፍ ስኬት ላስመዘገቡ አርሶና አርብቶ አደሮች እንዲሁም ባለድርሻዎች ዛሬ ዕውቅናና ሽልማት እየተሰጠ ነው።

እውቅናና ሽልማት እየተሰጠ ያለው ከ600 በላይ ለሚሆኑ አርሶና አርብቶ አደሮች ነው።

በተጨማሪም ከ80 በላይ ለሚሆኑ የምርምርና ግብርና ተቋማት እንዲሁም ግለሰቦችና ሙያተኞችም ሽልማትና እውቅና ይሰጣል።

የግብርና ምርት ላኪዎች፣ ዩንየኖች፣ መገናኛ ብዙሀንና ሌሎች ባለድርሻዎችም ይሸለማሉ።

የእውቅና አሰጣጥ ስነ ስርዓቱ ትናንት ከተከፈተው የዘመናዊ የግብርናና ፈጠራ ውጤቶች ኤግዚቢሽንና ባዛር የቀጠለ ነው ።

የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ ከፌደራልና ከክልሉ  የመንግስት የስራ ኅላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በእውቅና አሰጣጥ ስነ ስርአቱ ላይ እየተሳተፉ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም