ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዘጠነኛው ዙር 'ይቆጥቡ ይሸለሙ' መርሃ ግብር እድለኞች ሽልማታቸውን ተቀበሉ

ታህሳስ 22/2013 (ኢዜአ)የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዘጠነኛው ዙር 'ይቆጥቡ ይሸለሙ' መርሃ ግብር እድለኞች ሽልማታቸውን ተቀበሉ።

በአዲስ አበባ ዛሬ እየተካሄደ በሚገኘው የሽልማት ስነ ስርዓት ላይ በአዲስ አበባ የሚገኙ 2 አፓርታማ ቤቶች እጣው ለደረሳቸው እድለኞች ተላልፈዋል።

በተጨማሪም 3 መለስተኛ የጭነት ተሽከርካሪዎች፣ 15 የቤት አውቶሞቢሎችና 30 ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ለባለ እድለኞች ተሰጥተዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቤ ሳኖ በሽልማቱ ወቅት እንዳሉት መርሃ ግብሩ ላለፉት አስር ዓመታት የተካሄደ መሆኑን ገልጸው በዛሬው እለትም ዘጠነኛው ዙር የእጣ አወጣጥ መከናወኑን ተናግረዋል።

ፕሬዚዳንቱ አክለውም መርሓ ግብሩ የሕብረተሰቡ የቁጠባ ባህል እንዲያድግ እያስቻለ መሆኑንና ለአገሪቷ ኢኮኖሚ ልማትም ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ገልጸዋል።

በቀጣይም መርሃ ግብሩ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን የተናገሩት ፕሬዚዳንቱ ሕዝቡ ተሳትፎውን እንዲያጠናክርም ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም