ቀጥታ፡

ምርጫ ቦርድ ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች እንዲያሟሉ ከተጠየቁት መካከል አራቱ ፓርቲዎች መስፈርቱን ማሟላታቸውን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 19/2013 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በታህሳስ 13 ቀን 2013 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ መሰረት ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች እንዲያሟሉ ከተጠየቁት መካከል አራት ፓርቲዎች መስፈርቱን ማሟላታቸውን ገለጸ።

ሁለት ፓርቲዎች ደግሞ ባለማሟላታቸው መሰረዛቸውን ገልጿል።

መስፈርት በማሟላት ያጠናቀቁት የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር /ኦብነግ/- 39%፣ የአፋር ሕዝብ ፓርቲ /አሕፓ/- 45%፣ የጋሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ጋዴፓ/ -94% እና የአፋር ነፃ አውጭ ግንባር ፓርቲ /አነግፓ/ - 48% መሆናቸውን አመልክቷል።

የመላው ኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /መኦሕዴፓ/ የመስራች ፊርማ ናሙና ማረጋገጫ ከ35 % በታች በመሆኑ እና የ1 ሺህ 142 መሥራች አባላት የነዋሪነት ማረጋገጫ አይነት ያልተሟላ በመሆኑ መሰረዛቸውን ቦርዱ አስታውቋል።

እንዲሁም የሲዳማ ብሔራዊ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ /ሲብዴፓ/ - 778 መሥራች አባላት የነዋሪነት ማረጋገጫ አይነት ያልተሟላ በመሆኑ እና በምስክርም መረጋገጡ የቀረበ ነገር ባለመኖሩ መሰረዛቸው ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም