የ10 ዓመት ብሔራዊ የልማት ዕቅድ ሰላምን እና የሕግ የበላይነትን ወሳኝ ግቦች አድርጎ ማስቀመጡ ልዩ ያደርገዋል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ - ኢዜአ አማርኛ
የ10 ዓመት ብሔራዊ የልማት ዕቅድ ሰላምን እና የሕግ የበላይነትን ወሳኝ ግቦች አድርጎ ማስቀመጡ ልዩ ያደርገዋል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 19 /2013 (ኢዜአ) “የ10 ዓመት ብሔራዊ የልማት ዕቅድ ሰላምን እና የሕግ የበላይነትን ወሳኝ ግቦች አድርጎ ማስቀመጡ ልዩ ያደርገዋል” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት “ልማት ዘላቂ ሰላምን ያመጣል” ብለዋል።
የ10 ዓመት ብሔራዊ የልማት ዕቅድ ፍኖተ ብልጽግና ይህንን ከግምት ውስጥ ያስገባ መሆኑንም ገልጸዋል።
“ዕቅዱ ሰላምን እና የሕግ የበላይነትን ወሳኝ ግቦች አድርጎ ማስቀመጡ ልዩ ያደርገዋል” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ “በእነዚህ ፈታኝ ጊዜያትም እንኳ፣ ዘላቂ ሰላም እውን እንዲሆን የዜጎችን እና የተቋማትን የቅርብ ተሳትፎ የሚፈልጉ በርካታ ርምጃዎች እየተወሰዱ ይገኛሉ” ብለዋል።