የጉራጌ ዞን ሰባት ጎጎት ዶቢ ክስታኔ ሕዝብ ለመከላከያ ሠራዊት ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15 /2013 (ኢዜአ) በጉራጌ ዞን የሰባት ጎጎት ዶቢ ክስታኔ ማህበረሰብ ለአገር መከላከያ ሠራዊት 16 ሰንጋዎችና 20 ኩንታል ጤፍ ድጋፍ አበረከቱ፡፡

የማኅበረሰቡ ተወካዮች ዛሬ በምድር ኃይል ግቢ በመገኘት ድጋፉን አስረክበዋል።

በመከላከያ ሠራዊቱ ላይ የተፈፀመው ክህደት እንዳሳዘናቸው ተወካዮቹ ገልፀዋል።

የተደረገው ድጋፍ የአካባቢው ማኅበረሰብ ለሠራዊቱ ያለውን አጋርነት ለማሳየት መሆኑን የገለጹት ተወካዮቹ፤ ይህንኑ አጠናክረው ለመቀጠል ቃል ገብተዋል፡፡

የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ማርታ ሊዊጂ ድጋፉን ከተረከቡ በኋላ ማኅበረሰቡ ለሠራዊቱ ላበረከተው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ሠራዊቱ ከሕዝቡ እየተደረገለት ያለው ድጋፍ የሞራል ስንቅ ሆኖት ተልዕኮውን በድል መወጣቱንና ለወደፊቱም በልማት እንደሚደግመው አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም