የሕግ ጥሰቶች የፈጸሙ ሁለት አትሌቶች የቅጣት ውሳኔ ተላለፈባቸው - ኢዜአ አማርኛ
የሕግ ጥሰቶች የፈጸሙ ሁለት አትሌቶች የቅጣት ውሳኔ ተላለፈባቸው
አዲስ አበባ ታህሳስ 14/2013 (ኢዜአ) የስፖርት አበረታች ቅመሞች፤ የሕግ ጥሰቶች የፈጸሙ ሁለት አትሌቶች ላይ የቅጣት ውሳኔ መተላለፉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ የጸረ-አበረታች ቅመሞች ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
አትሌት ወንድወሰን ከተማ ማሞ እና አትሌት እዮብ ኃብተስላሴ ጎሳ የስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ የሕግ ጥሰቶችን በመፈፀም ተጠርጥረው ጊዜያዊ እገዳ ላይ ሆነው ጉዳያቸው ሲጣራ ቆይቷል።
በዚሁ መሰረት በተደረገ ተጨማሪ ምርመራ አትሌት እዮብ ኃብተስላሴ ጎሳ ጥር 24 ቀን 2013 ዓ.ም በታይላንድ በተካሄደ ውድድር ላይ "ካቲነን" (Cathinone) የተባለውን የተከለከለ የስፖርት አበረታች ቅመም መጠቀሙ እንደተረጋገጠ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ የጸረ-አበረታች ቅመሞች ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
አትሌቱ ከመጋቢት 25 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ አራት ዓመታት በማንኛውም ውድድር ላይ እንዳይሳተፍ ቅጣት የተጣለበት ሲሆን በውድድሩ የተገኘው ውጤትና ውጤቱን ተከትሎ የሚሰጥ የእውቅና ሽልማትም እንዲሰረዝ መወሰኑን ገልጿል።
በተመሳሳይ አትሌት ወንድወሰን ከተማ ማሞ ቀደም ሲል "ካቲነን" (Cathinone) የተባለውን የተከለከለ የስፖርት አበረታች ቅመም መጠቀሙ በመረጋገጡ እ.ኤ.አ እስከ ፌብሩዋሪ 1 ቀን 2024 ድረስ በማንኛውም ውድድር ላይ እንዳይሳተፍ እገዳ ተጥሎበት ነበር።
ይሁን እንጂ አትሌቱ የተሳሳቱ የሰነድ ማስረጃዎችን በማቅረብ የሕግ ጥሰቱን የማጣራት ሂደቱን በተለያየ መልኩ በማስተጓጎልና በድጋሚ ለማጭበርበር በመሞከር ተደራራቢ የህግ ጥሰት በመፈፀም ተጠርጥሮ ጉዳዩ መቆየቱን ጽህፈት ቤቱ በመግለጫው አመልክቷል።
በመሆኑም አትሌት ወንድወሰን ያቀረባቸው ሰነዶች የሐሰት መሆናቸው በመረጋገጡና በጸረ-ዶፒንግ ሕጉ አንቀፅ 2.5 ላይ የተደነገገውን የጸጸረ-ዶፒንግ እንቅስቃሴውን የማስተጓጎልና አቅጣጫ የማሳት የሕግ ጥሰት መፈፀሙ በመረጋገጡ ቀደም ሲል ከተጣለበት የአራት (4) አመት የእገዳ ቅጣት በተጨማሪ የመጀመሪያው ቅጣት ከሚያበቃበት እ.አ.አ ፌብሩዋሪ 1,2024 ጀምሮ ተጨማሪይ ስምንትተከታታይ ዓመታት እስከእ.አ.አ ፌብሩዋሪ 1ቀን 2032 በማንኛውም ስፖርታዊ ውድድር ላይ እንዳይሳተፍ የእገዳ ቅጣት ተላልፎበታል።
የኢትዮጵያ ሔሄራዊ ጸፀረ-አበረታች ቅመሞች ህፈት /ቤት በቀጣይም የምርመራና ቁጥጥር ስራውን አጠናክሮእንደሚቀጥል አስታውቋል።፡