ኢትዮጵያ ሁለተኛ ሳተላይት አመጠቀች - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ ሁለተኛ ሳተላይት አመጠቀች

ታህሳስ 13/2013 ( ኢዜአ) ኢትዮጵያ ET-Smart-RSS የተባለች ሳተላይት ማምጠቋን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።
ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት ETRSS-1 የተባለች የመጀመሪያዋን የመሬት ምልከታ ሳተላይት ታኅሣሥ ወር 2012 ዓ.ም ማምጠቋ ይታወሳል።
ባለፈው አመት የመጠቀችው “ETRSS-1” የሚል ስያሜ የተሰጣት ምድርን እየቃኘች ፎቶ እየመዘገበች መረጃ የምትሰበስበው ሳተላይት በሀገራችን የዕድገት ጉዞ ላይ ቁልፍ ሚና እንደሚኖራት መነገሩ አይዘነጋም።
መረጃ መላክ የጀመረችው ይች ሳተላይት የአየር ንብረት ለውጥን ለመቆጣጠር፣ ከግብርና ጋር የተያያዙ ጥናት እና ምርምሮችን ለመሥራት እና ሌሎች ዘርፈ ብዙ የመሠረተ ልማት ተግባራትን በማከናወን ላይ ትገኛለች።
ኢትዮጵያ አሁን ደግሞ ET-Smart-RSS የተባለች ሳተላይት ማምጠቋን ነው ኢንስቲትዩቱ ያስታወቀው።