በኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የተቋቋመው "ኢትዮጵያ ትቀጥላለች" የሚባለው የሲቪክ ማህበረሰብ ተቋም 15 ሺህ ዶላር ሰብአዊ ድጋፍ አደረገ - ኢዜአ አማርኛ
በኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የተቋቋመው "ኢትዮጵያ ትቀጥላለች" የሚባለው የሲቪክ ማህበረሰብ ተቋም 15 ሺህ ዶላር ሰብአዊ ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 12 / 2013 (ኢዜአ) በአሜሪካ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የተቋቋመው "ኢትዮጵያ ትቀጥላለች" የሚባለው የሲቪክ ማህበረሰብ ተቋም በኢትዮጵያ ሰብአዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች የሚውል 15 ሺህ ዶላር ድጋፍ አደረገ።
"ኢትዮጵያ ትቀጥላለች" በሚል መሪ ሃሳብ የተዘጋጀ የበይነ መረብ ትናንት በተካሄደው ውይይት ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች፣ አምባሳደሮች፣ ታዋቂ ግለሰቦችና የዳያስፖራ አባላት ተሳትፈዋል።
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር መሐመድ እንድሪስ "ኢትዮጵያ ትቀጥላለች" የሚለው እሳቤ የግዛት ቀጣይነትን ብቻ ሳይሆን እሳቤው የአገረ መንግስትና የተቋማት እንዲሁም ማህበረሰቡን ያስተሳሰሩት እሴቶች ተጠብቆ ማቆየት መሆኑን ገልጸዋል።
በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለአገራዊ አንድነትና ትልሞች መሳካት እያደረጉት ላለው አዎንታዊ አስተዋጽኦም ምስጋና አቅርበዋል።
በተለይም መድረኩን ላመቻቸውና በአሜሪካ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለተመሰረተው "ኢትዮጵያ ትቀጥላለች" የሲቪክ ማህበረሰብ ተቋም አመስግነዋል።
በውይይት መድረኩ ላይ ተቋሙ በኢትዮጵያ ሰብአዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች 15 ሺህ ዶላር ድጋፍ ማድረጉ ተገልጿል።