የኢጋድ አባል ሀገራት መሪዎች መንግስት የወሰደውን የህግ ማስከበር እርምጃ ህጋዊነት በመረዳታቸው ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አመሰገኑ

49

ታህሳስ 11/2013 (ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ የኢጋድ አባል ሀገራት መሪዎች መንግስት የወሰደውን የህግ ማስከበር እርምጃ ህጋዊነት በመረዳት እውቅና በመስጠታቸው ምስጋና አቀረቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ''የኢጋድ አባል ሀገራት መሪዎች የህግ ማስከበር እርምጃችንን እንደ ህጋዊነት በመረዳታቸውና እውቅና በመስጠታቸው አመሰግናለሁ'' ብለዋል።

መሪዎቹ ጁቡቲ እየተካሄደ በሚገኘው 38ኛው አስቸኳይ የኢጋድ የመሪዎች ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ ነው።

በዚሁ ጉባኤ ላይ ከመሪዎቹ ጋር የተወያዩት ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ መሪዎቹ በዚህ ረገድ ኢትዮጵያን ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆናቸውን በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ ከሳምንት በፊት በኬንያ ጉብኝት ማድረጋቸውን ተከትሎ ከፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር ውይይት ማድረጋቸው ይታወሳል።

ዛሬም ጅቡቲ እያስተናገደች በሚገኘው 38ኛው ጉባኤ ጎን ለጎን ከፕሬዝዳንት ኡሁሩ ጋር በቀጣናዊ እና በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም