በወላይታ ሶዶ መርካቶ የገበያ ማዕከል ላይ የእሳት አደጋ ደረሰ - ኢዜአ አማርኛ
በወላይታ ሶዶ መርካቶ የገበያ ማዕከል ላይ የእሳት አደጋ ደረሰ
ሶዶ፣ ታህሳስ 11/2013 (ኢዜአ) በወላይታ ሶዶ ከተማ በተለምዶ መርካቶ እየተባለ በሚጠራው የገበያ ስፍራ ዛሬ ማለዳ ላይ የእሳት አደጋ ደረሰ።
የከተማ አስተዳደሩ የከንቲባ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ፍስሀ ጸጋዬ ለኢዜአ እንደገለጹት ዛሬ ማለዳ አንድ ሰዓት ላይ የተነሳው ቃጠሎ እስከ አሁን በቁጥጥር ስር ለማዋል እየተሰራ ነው።
የከተማው ነዋሪዎች እንዲሁም የፖሊስ አባላት ቃጠሎውን ለማጥፋት ርብርብ እያደረጉ ይገኛል።
በከተማዋ ማዘጋጃ ቤት የእሳት መከላከያ እሳቱን ለማጥፋት ጥረት እያደረገ ቢሆንም አሁን ባለው ነፋሻማ አየር ጸባይ ምክንያት የመቆጣጠር ስራውን ፈታኝ እንዳደረገውም ተናግረዋል።
በቃጠሎው ምክንያት የደረሰው የጉዳት መጠን አጠቃላይ የመከላከል ስራው እንደተጠናቀቀ በዝርዝር የሚገለጽ መሆኑም ተመልክቷል።