ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቦርድ አመራሮችን ሹመት አጸደቀ - ኢዜአ አማርኛ
ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቦርድ አመራሮችን ሹመት አጸደቀ
አዲስ አበባ ሐምሌ 13/2010 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቦርድ አመራሮችን ሹመት አጸደቀ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ የይቅርታና የምህረት አዋጁን ከማጽደቅ በተጨማሪ የፕሬስ ድርጅት የቦርድ አባላትን ምርጫ አጽድቋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለምክር ቤቱ አባላት ባቀረቡት ዝርዝር መሰረት የድርጅቱን ስምንት የቦርድ አመራር አባላት በሙሉ ድምፅ ፀድቋል። በዚህ መሰረት አቶ ካሳሁን ጎፌ የቦርድ ሰብሳቢ ፣ወይዘሮ ጀሚላ ሺምቢሩ፣ ወይዘሮ አበበች ሺከቻ፣ አቶ በቀለ ሙለታ፣ አቶ ዮናስ አስናቀ፣ አቶ ወንድወሰን አንዷለም፣ አቶ ተካ አባዲና ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በአባልነት ተመርጠዋል። የድርጅቱ የቦርድ አመራሮችም በምክር ቤቱ አባላት ፊት ቃለ መሃላ ፈፅመዋል።