የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በመቀሌ ከመንግሥት ሠራተኞች ጋር ተወያየ

69

አዲስ አበባ ታህሳስ 6/2013 (ኢዜአ) የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር መቀሌ ከሚገኙ የመንግሥት ሠራተኞች ጋር ተወያየ።

ሠራተኞቹ ከትናንት ጀምሮ ወደ መደበኛ ሥራቸው ተመልሰዋል።

በውይይቱ የተሳተፉት ሠራተኞች በሕግ ማስከበር ሂደቱ ከአንድ ወር በላይ በቤታቸው መቆየታቸውን ተናግረዋል፡፡

የመንግስት ሠራተኛ የሕዝብ አገልጋይ እንጂ የፖለቲካ ዓላማ አራማጅ እንዳልሆነ የተናገሩት ሠራተኞች ወደ መደበኛ ስራቸው ለመመለስ ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡

በመቀሌ የሰፈነው ሠላም ስራቸውን በአግባቡ ለመከወን እንደሚያስችላቸውም ተናግረዋል፡፡

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተደዳር ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ ከውይይቱ በኋላ በሰጡት መግለጫ ጊዜያዊ አስተዳደሩ የመንግስት ሠራተኞችን ወደ ስራ ለመመለስ ጥሪ ማቅረቡን አስታውሰዋል፡፡

በጥሪው መሰረት ሠራተኞቹ ከትናንትና ጀምሮ ወደ መደበኛ ስራቸው የተመለሱ ሲሆን በተለመደው አግባብ ሕዝቡን ለማገልገል ስምምነት ላይ መደረሱንም ገልጸዋል፡፡

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የመንግስት ሠራተኞች እስከ ታህሳስ 5 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ወደ መደበኛ ስራቸው እንዲመለሱ ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም