በቶኪዮ ኦሎምፒክ በአትሌቲክስ ስምንት ሜዳሊያዎችን ለማግኘት ታቅዷል - ኢዜአ አማርኛ
በቶኪዮ ኦሎምፒክ በአትሌቲክስ ስምንት ሜዳሊያዎችን ለማግኘት ታቅዷል
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6/2013 ( ኢዜአ) በቶኪዮ ኦሎምፒክ በአትሌቲክስ ውድድር ስምንት ሜዳሊያዎችን ለማግኘት ማቀዱን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።
የኢትዮጵያ አትሌትክስ ፌዴሬሽን 24ኛ ጠቅላላ መደበኛ ጉባኤውን አካሂዷል።
የፌዴሬሽኑ የጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ቢልልኝ መቆያ በጉባኤው ላይ እንደገለጹት በዚህ ዓመት በሚካሄደው የቶኪዮ ኦሊምፒክ 36 አትሌቶችን በአትሌቲክስ ስፖርት ለማሳተፍ ታቅዷል።
በዚህ የኦሎምፒክ ስፖርት ከሚሳተፉ አትሌቶች 2 ወርቅ፣ 2 ብርና 4 የነሐስ ሜዳሊያ ለማግኘት መታቀዱንም ነው የገለጹት።
አሁን ላይ ከ100 በላይ አትሌቶች ተመርጠው ለውድድሩ በዝግጅት ላይ መሆናቸውንም ተናግረዋል።
ከእነዚህ አትሌቶች መካከል የተሻለ ብቃት ያላቸው 36 አትሌቶች ተመርጠው የውድድሩ ተሳታፊ ይሆናሉ ተብሏል።