ቀጥታ፡

የትግራይ ክልል የአየር መሥመር ለአገልግሎት ክፍት ሆነ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 5/2013 (ኢዜአ) ለጊዜው ተቋርጦ የነበረው ወደ ትግራይ ክልል የሚደረግ የአየር መሥመር አገልግሎት ክፍት መሆኑን የኢትዮጵያ ሲቭል አቪዬሽን ባለስልጣን አስታወቀ።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል የህግ ማስከበር ሂደትን ተከትሎ ተዘግቶ የነበረው የአየር ክልል ከዛሬ ጀምሮ ክፍት ሆኗል ብሏል።

በሰሜን የኢትዮጵያ የአየር ክልል ውስጥ የሚያቋርጡ የአለም አቀፍ እና የሃገር ውስጥ የበረራ መስመሮች ለአገልግሎት ክፍት መሆናቸው ታውቋል።

በመሆኑም አገልግሎት መሥጠት የሚችሉ ኤርፖርቶች በረራ ማስተናገድ የሚችሉ መሆኑን ነው ከባለስልጣኑ የተገኘው መረጃ የሚጠቁመው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም