የኢትዮጵያ አትሌቲክስ የይቻላል መንፈስን በዓለም መድረክ ላይ ከፍ አድርጎ ያሳየ ነው - ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ የይቻላል መንፈስን በዓለም መድረክ ላይ ከፍ አድርጎ ያሳየ ነው - ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ
ታህሳስ 3/2013 ዓ.ም (ኢዜአ) “የኢትዮጵያ አትሌቲክስ የይቻላል መንፈስን በዓለም መድረክ ላይ ከፍ አድርጎ ያሳየ ነው” ሲሉ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በለገጣፎ ለገዳዲ ያስገነባው የአትሌቲክስ ስፖርት አሸዋ ትራክ ተመርቋል።
የአትሌቲክስ ስፖርት አሸዋ ትራኩ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ ፣ የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኤሊያስ ሽኩር፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተ/ም/ ፕሬዚዳንት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ እና የለገጣፎ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወይዘሮ ሀቢባ ሲራጅ በተገኙበት ተመርቋል።
የኦሮሚያ ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ “የኢትዮጵያ አትሌቲክስ በዓለም መድረክ ላይ የይቻላል መንፈስን ያሳየ ነው” ብለዋል።
በመሆኑም የክልሉ መንግስት የእትሌቲክስ ስፖርትን በመደገፍ በኩል አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።
በለገጣፎ ለገዳዲ የተገነባውን የአትሌቲክስ ማዘውተሪያ ዓይነት በሰበታ፣ በቡራዩና በሱሉልታ በክልሉ መንግስት፣ በስፖርት ኮሚሽንና በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ትብብር እንደሚገነባ ጠቁመዋል።