ጂቡቲ ከኤርትራ ጋር ያላትን የድንበር ውዝግብ ለመፍታት የተመድን እርዳታ ጠየቀች

34
አዲስ አበባ ሀምሌ 12/2010 ጂቡቲ ከኤርትራ ጋር ያላትን የድንበር ውዝግብ ለመፍታት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንዲያሸማግላት በይፋ ጠየቀች። በመንግሥታቱ ድርጅት የጂቡቲ አምባሳደር ሞሃመድ ሰይድ ዶዋለህ ትናንት ይህንን ጥያቄ ለድርጅቱ በደብዳቤ ማቅረባቸውን አረጋግጠዋል። "ጂቡቲ የድንበር ውዝግቡን ለመፍታት የፍርድ ቤት ውሳኔ ወይንም አሸማጋይ ትፈልጋለች" ማለታቸውን አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል። የራስ ዱሜራ ግዛትን ውዝግብ ለመፍታት ባለፉት ሰባት ዓመታት የኳታር የሰላም አስከባሪ ወታደር በስፍራው ላይ ቆይቷል። ይሁንና የኳታር የሠላም ጥረት ባለመሳካቱ ከወራት በፊት 450 የሚጠጉ ወታደሮቿን ከስፍራው አስወጥታለች። ከዚያ በኋላ ስፍራውን ኤርትራ መቆጣጠሯን በመግለጽ ጂቡቲ ለአፍሪካ ህብረትም ቅሬታዋን ማቅረቧ ይታወሳል።      
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም