ለ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የክለሳ ትምህርት በቴሌቪዥን ፕሮግራም ተጀመረ - ኢዜአ አማርኛ
ለ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የክለሳ ትምህርት በቴሌቪዥን ፕሮግራም ተጀመረ

አዲስ አበባ ታህሳስ 2/2013 (ኢዜአ) የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለሚወስዱ ተማሪዎች ተቋርጦ የነበረውን ትምህርት መከለስ የሚያስችል የቴሌቪዥን ፕሮግራም መጀመሩን ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ፡፡
በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተቋርጦ የቆየው የገጽ ለገጽ ትምህርት መጀመሩ ይታወቃል።
ሚኒስቴሩ እንደገለፀው የ12ኛ ክፍል ፈተና ለሚወስዱ ተማሪዎች ተቋርጦ የነበረውን ትምህርት መከለስ የሚያስችል የቴሌቪዥን ፕሮግራም ተጀምሯል።
በዚሁ መሰረት እንግሊዘኛ፣ ሒሳብ፣ ኬሚስትሪ፣ ፊዚክስ፣ ባዮሎጂ፣ ጂኦግራፊና ኢኮኖሚክስ ትምህርቶች በኢትዮጵያ ትምህርት በቴሌቪዥን ጣቢያ /MOE-TV/ ከሰኞ እስከ እሁድ በድግግሞሽ ይተላለፋል ብሏል።
ተማሪዎች በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ትምህርት እንዲከታተሉና ወላጆችም አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው ሚኒስቴሩ ጥሪ አቅርቧል፡፡
የቴሌቪዥን ትምህርት ፕሮግራምና የስርጭት የጊዜ ሰሌዳ በተለያዩ አማራጭ የመገናኛ ብዙሃን እንደሚገኝ ገልጿል።
የስርጭት የጊዜ ሰሌዳውንና የተዘጋጁትን ፕሮግራሞች Portal – www.eict.edu.et Youtube -Educational Plasma Programs Grade 11-12, Telegram - የኢትዮጵያ ትምህርት በቴሌቪዥን /MOE-TV/ በአማራጭነት ማግኘት እንደሚቻልም ጠቁሟል