የአዲስ ብድርና ቁጠባ ተቋም ሰራተኞችና አመራሮች ለመከላከያ ሰራዊት ከ6 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ - ኢዜአ አማርኛ
የአዲስ ብድርና ቁጠባ ተቋም ሰራተኞችና አመራሮች ለመከላከያ ሰራዊት ከ6 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1/2013 (ኢዜአ) የአዲስ ብድርና ቁጠባ ተቋም ሰራተኞች ህግ በማስከበር ሂደት ላይ ለተሰማራው የአገር መከላከያ ሰራዊት ከ6 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ፡፡
የተቋሙ ሰራተኞች በሰሜን እዝ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ የህግ ማስከበር ዘመቻውን አጠናቆ ወንጀለኞችን በማደን ተግባር ላይ ለተሰማራው የአገር መከላከያ ሰራዊት ያላቸውን ድጋፍ ገልጸዋል።
የተቋሙ አመራርና ሰራተኞች ለሰራዊቱ ያላቸውን አጋርነት ለማሳየትም የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለግሰዋል።
በዚህም 6 ሚሊዮን 468 ሺህ ብር ድጋፍ ማድረጋቸውን አስታውቀዋል።