ቀጥታ፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ አስቸኳይ ስብሰባ ያካሂዳል

ሃምሌ 12/2010 የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባውን በነገው እለት ያካሂዳል። ምክር ቤቱ ነገ ሐምሌ 13 ቀን 2010 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በሚያካሂደው አስቸኳይ ስብሰባው፡- የም/ቤቱን 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 5ኛ ልዩ እና 6ኛ ልዩ ስብሰባዎች ቃለ ጉባኤ መርምሮ ያጸድቃል፤የህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በተለያዩ የወንጀል ድርጊት የተሳተፉ ሰዎች ምህረት ለመስጠት የቀረበ ረቂቅ አዋጅ በተመለከተ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ ያጸድቃል፣ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የተጓደሉ የስራ አመራር ቦርድ አባላትን ለመሾም የቀረበ የውሳኔ ሃሳብንም መርምሮ እንደሚያጸድቅ ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም