18 የተለያዩ ባንኮች ለመከላከያ ሰራዊት የ200 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረጉ - ኢዜአ አማርኛ
18 የተለያዩ ባንኮች ለመከላከያ ሰራዊት የ200 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረጉ
አዲስ አበባ ህዳር 30/2020 (ኢዜአ) በኢትዮጵያ የሚገኙ 18 የተለያዩ መንግስትና የግል ባንኮች ለመከላከያ ሰራዊት የ200 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረጉ።
ከባንኮች በተጨማሪ የኢትዮጵያ መድን ድርጅት የ5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ፣ አዋሽ ባንክ፣ አቢሲኒያ ባንክ፣ ዳሽን ባንክ፣ አባይ ባንክ፣ እናት ባንክ፣ ዘመን ባንክ፣ ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ፣ ኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ፣ ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ፣ ወጋገን ባንክ፣ ብርሃን ባንክ፣ ቡና ባንክ፣ ህብረት ባንክ አዲስ ኢንተርናሽናል እና ደቡብ ግሎባል ባንኮች ናቸው።
በግጋፉም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 100 ሚሊዮን ብር ለግሷል።
አዋሽ፣ ዳሽን፣ አቢሲኒያ፣ የኦሮሚያ ህብረት ስራ፣ ልማትና ህብረት ባንኮች እያንዳንዳቸው የ10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርገዋል።
ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል፣ ብርሃን፣ ዘመን፣ንብ ኢንተርናሽናል ባንኮች እያንዳንዳቸው የ5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደርገዋል።
በተመሳሳይ የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ለአገር መከላከያ ሰራዊት የ5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል።
አባይ፣ ወጋገን፣ ደቡብ፣ ቡና፣ እናት ባንኮች እያንዳንዳቸው 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርገዋል።
ድጋፉን የኢትዮጵያ ባንኮች ማህበር ፕሬዝዳንት አቢ ሳኖ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አበቤ ያስረከቡ ሲሆን ምክትል ከንቲባዋም ለአገር መከላከያ ሰራዊት ተወካይ ኮሎኔል የኑስ ሙሉ አስረክበዋል።