የኮንሶ ዞን ነዋሪዎች ለአገር መከላከያ ሠራዊት 368 ፍየሎችን አበረከቱ - ኢዜአ አማርኛ
የኮንሶ ዞን ነዋሪዎች ለአገር መከላከያ ሠራዊት 368 ፍየሎችን አበረከቱ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 30/2013 (ኢዜአ) የኮንሶ ዞን ነዋሪዎች ለአገር መከላከያ ሠራዊት ድጋፋቸውን ለመግለጽ 368 ፍየሎችን አበረከቱ።
የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበየው የኮንሶ ዞን ነዋሪዎች ለአገር መከላከያ ሠራዊት ያላቸውን አጋርነት ለማሳየት ድጋፉን ማበርከታቸውን ተናግረዋል።
“በሚቀጥሉት ጊዜያት የኮንሶ ሕዝብ ለአገር መከላከያ ሰራዊት በገንዘብ፣ በሞራልና በጉልበት ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ነው” ብለዋል።
ድጋፉን የተቀበሉት የመከላከያ ሚኒስቴር የፋይናንስ ስራ አመራር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ማርታ ሉዊጂ ለዞኑ ነዋሪዎች ምስጋና አቅርበዋል።
“መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሠራዊቱን በመደገፍ ያደረውን ርብርብ በየተሰማራባቸው መስኮች በመድገም ለአገር ሠላም መከበርና ዕድገት መረባረብ ያስፈልጋል” ብለዋል።