ቀጥታ፡

እኩይ ተልዕኮ ተሸክሞ ሲንቀሳቀስ የነበረው የህወሓት ሃይል ተወግዶ በዓሉ መከበሩ ቀኑን ልዩ ያደርገዋል

አዲስ አበባ ህዳር 29/2013 (ኢዜአ) የዘንድሮው የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል ህዝቦችን በማናከስ እኩይ ተልዕኮ ተሸክሞ ሲንቀሳቀስ የነበረው የህወሓት ሃይል ተወግዶ መከበሩ ልዩ ያደርገዋል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለጹ።

15ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፤ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል የአገር አቀፍ ሲምፖዚየም መርሐግብር እየተካሄደ ነው።

በመርሐግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የኢትዮጵያ ብሔሮች፤ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ራሳቸውን ችለው በልዮ ውበት የሚፈሱ ወንዞች ናቸው።

ይሕም ውበታቸው ሕብረ ብሔራዊነትን የያዘ የአንድነት መገለጫ ነው ብለዋል።

በዓሉም የኢትዮጵያ ብሔሮች፤ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ውበት ማሳያ ነው ብለዋል።

የዘንድሮውን የኢትዮጵያ ብሔሮች፤ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓልልዮ የሚያደርገው ደግሞ ህዝቦችን በማናከስ እኩይ ተልዕኮ ተሸክሞ ሲንቀሳቀስ የነበረው የህወሓት ሃይል ተወግዶ መከበሩ ነው ብለዋል።

ይህንን እኩይ ሓይል ለማስወገድ ዋጋ ለከፈሉ የጸጥታ ሀይሎችና ዜጎችም ምስጋና አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም